የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባለው በጀት የስቴሽነሪ፣ የዕዳት እቃዎች; የመኪና መለዋወጫ፡ የአይቲ፤ እንዲሁም ሌሎች የቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ እና አገልግሎቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
PTC: ECMA/NCB/10/2018
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባለው በጀት የስቴሽነሪ፣ የዕዳት እቃዎች; የመኪና መለዋወጫ፡ የአይቲ፤ እንዲሁም ሌሎች የቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ እና አገልግሎቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር በመክፈል ከባለሥልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ከፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡
2 ተጫራቶች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴከኒካል አሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
3.ተጫራቶች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፤ የግብር ከሊራንስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማኅተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4- ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለሥልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው፡፡
6. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማኅተምና የተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል፡፡
7. አሸናፈው ተጫራች እቃዎችን እንዲሁም አገልግሎቶችን በራሱ ትራንስፖርት ባለሥልጣኑ ዋ/መ/ቤት የማምጣት እና የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡
8 ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያነት የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒአ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
9 ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሠረት በማድረግ የሚያቀርቡትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዝርዝርየቴከኒከ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
10- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
11. ጨረታው ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በ9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ9፡30 ላይ ተጫራቶችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
12. በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቶች አለመኖር የጨረታውን መከፈት እያስተጓጉለውም፡፡
13. ባለሥልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚጎ ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ምናዊ ኮርፖረት ቢሮ ፓርክ ክ/ከተማ ቂርቆስ፣ ወረዳ 9 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ 011-5-57-83-27
ኢሜል፡Procurement@ecma.gov.et
የሩይናንስና ግዥ ዳይሬክተሬት
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባስስልጣን
