በደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክ/መ/በካፋ ዞን ቢጣ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2018ዓ.ም ለወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክ/መ/በካፋ ዞን ቢጣ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2018ዓ.ም ለወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡ - በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች:-
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በመስከ- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና ደረጃቸው GC/BC ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
2. የአቅራብነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
3. የብቃት ማረጋገጫ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የግብር ከፋይነት መለያ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. የመንግስት ግብር ዕዳ ስላለመኖሩ /ታክስ ክሊራንስ/ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. ከሚያገኘው ገቢ ለመንግስት 2% ለመከፈል ፍቃደኛ የሆኑ::
7. ማንኛውም ተጫራች ሠነድ ከመግዛቱ በፊት ከአሰሪው መ/ቤት በመቅረብ የግንባታውን ሣይት ሁኔታ መረጃ መውሰድ አለበት፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ጠቅላላ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒዎችን እና ማመልከቻ ይዞ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ በማይመለስ 500ብር (አምስት መቶ) የኢትዮጵያ ብር ብቻ ከፍሎ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
10. የጨረታ ማስከበሪያ 110000ብር (አንድ መቶ አስር ሺህ ብር)ብቻ ሁኔታ ላይያልተመሠረተ የባንክ ሲፐኦ ወይም በካሽ ከኦርጅናል ቴከኒካል ዶክመንት ጋር በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሠነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማመሳከር ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ /በፖስታ/ በማሸግ እንዲሁም SBD ለብቻ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
12. ጨረታው በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ30 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ31ኛ የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታው ሂደት የማይስተጓገል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ኣማራጭ ካገኛ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ለበለጠ መረጃ:- በ0477730018/17/19 ደውስው ይጠይቁን
በደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክ/መ/በካፋ ዞን ቢጣ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት
