የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን ለቢሮ መገልገያ የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ማሽኖች ብልሽት በሚያጋጥማቸው ወቅት ጥገና ማከነወን የሚችሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለአንድ ዓመታት ውል በመዋዋል ማሠራት ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር AAWSA/WSIDD/GOV/NCB/NCS001/2018
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን ለቢሮ መገልገያ የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ማሽኖች ብልሽት በሚያጋጥማቸው ወቅት ጥገና ማከነወን የሚችሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለአንድ ዓመታት ውል በመዋዋል ማሠራት ይፈልጋል፤
- ምድብ አንድ፡- የዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒዮተር ጥገና እና ሰርቪስ፣
- ምድብ ሁለት፡- የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና እና ሰርቪስ፣
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አገልግሎት አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ልደታ በሚገኘው የሕዝብ መናፈሻ ጎን የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ በሚገኘው የዲቪዥኑ ቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድርስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት መወዳደሪያ ፖስታው ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፤
- በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ የጨረታ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) ለእያንዳንዱ ምድብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሠነድ ጋር በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፤
- አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ/ ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታል፤
- የተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ለ60 /ለስልሣ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፤
- የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፤
- ጨረታው ታህሳስ 15/2018ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ8፡30 5ኛ ፎቅ ዲቪዥኑ ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳዳሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤
- እያንዳንዱ ተጫራች ዲቪዥኑ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት፡፡ ይህንን ያልገለፀ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፤
- ዲቪዥኑ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን የአገልግሎቶች ግዥ በ 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዲቪዥኑ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08፣ የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ
ስልክ ቁጥር:- +251 11 5579512/9036 (1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል)
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
