Tender Detail

Tender Details

  • Company በአ.ብ.ክ.መ. የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል
  • Address ዓለም ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913 089 057
  • Website
  • Deadline09 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-12-09 00:00:00
  • Categories Office Equipment

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል የ2018 ዓ/ም የበጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የቢሮ እቃዎች የግልፅ ጨረታ እወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል፡፡

በአ.ብ.ክ.መ. የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል የ2018 ዓ/ም የበጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የቢሮ እቃዎች የግልፅ ጨረታ እወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል፡፡

የእቃዎች ዝርዝር

የፅዳት እቃዎች እና የህትመቶች፣ የኤሌክትሮኒከስ፣የደንብ ልብስ፣የፕላስቲክውጤቶች፣የቧንቧ እቃዎች፣የፅህፈት መሳሪያዎች፣የህንፃ መሳሪያ፣ኮምፒውተርና ተዛማጅ፣ የመኪና እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ

2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነበር/ ተመዝጋቢና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችልሉ

4. ጠቅላላ ግዥው ወይም ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ መሆኑ ሲገመት ተጫራቾች /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከርሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍና የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከላይ በተ.ቁ ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውንና ኦርጅናል ሰነዶቻቸውን ማቅረብና ማመሳከር ይኖርባቸዋል

6. ጥራት ያላቸውና ኦርጅናል እቃዎችን ማቅረብ የሚችል

7. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነና ለመለየት አሻሚ ከሆነ ዋጋ አይኖረውም

8. ተጫራቾች ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/በመከፈል ዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሰ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ለመ/ቤቱ ደረሰኝ አለባቸው፡፡

10. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ 1 ወጥ ወይም ሁለት ወጥ ፖስታዎች በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደርየሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. የጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም/ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡01 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡10 ላይ ይከፈታል::

12. ተጫራቾች ለእቃው ዓይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ መሳተፍ ይኖርባቸዋል ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም፡፡ ማለት በሎት በሚወዳደርበት ሰዓት ያልሞላው ዋጋ ካለ ውድቅ ነው፡፡

13. መ/ቤታችን በሚገዛው እቃ ላይ 20% መቀነስ 30% መጨመር ይችላል

14. ለደንብ ልብሶችና የፅዳት ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዓ/ከ/እ/ጠ/ሆ/ግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር0111320741 ወይም በስልክ ቁጥር 0913089057/0921211083 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

17. የጨረታው መከፈቻ በበአላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይሰአት የሚከፈት ይሆናል ፡፡

18. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ በሎትም ሆነ በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው

19. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉበትን እቃ የአሸናፊነት ደብዳቤ በተሰጣቸው መሰረት ሁሉንም ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከላይ የተዘረዘሩት የተጫራቾች መመሪያ ከአጠቃላይ የተጫራቾች ዝርዝር መመሪያዎች በከፊል የተወሰዱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል

Save Tender