Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline22 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-22 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ GC/BC-4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በደምቢ ዶሎ እና በነቀምት ኤርፖርቶች የፈዴራል ፖሊስ መኖሪያ ህንፃዎች ግንባታ ፕሮጀክት (For construction of New Federal Police Residence Building at Dembi Dolo and Nekemte Airports.) ለማሠራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T586

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ GC/BC-4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በደምቢ ዶሎ እና በነቀምት ኤርፖርቶች የፈዴራል ፖሊስ መኖሪያ ህንፃዎች ግንባታ ፕሮጀክት (For construction of New Federal Police Residence Building at Dembi Dolo and Nekemte Airports.) ለማሠራት ይፈልጋል።

  1. ስለሆነም ለሥራው ብቁ የሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እና የህንፃ ሥራ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን: የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣ ፕሮጀክቶቹን የማጠናቀቂያ ጊዜ 180 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ይሆናል::
  2. የፌዴራል ፖሊስ መኖሪያ ቤት በሁለት ብቁ ተቋራጮች ሊያስገነባ ይፈልጋል፣ ፕሮጀክቱ በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ተከፍሏል። LOT-1 ሁለት አዲስ የፌዴራል ፖሊስ መኖሪያ በደምቢ ዶሎ እየር ማረፊያ፣ & LOT-2: ሁለት አዲስ የፈዴራል ፖሊስ መኖሪያ በነቀምቴ ኤርፖርት።
  3. አንድ ተጫራች በአንድ LOT ላይ ብቻ እንዲሳተፍ ይጠበቃል። ተጫራቹ ለመረጠው LOT ብቻ ዋጋ (proposal) ማቅረብ ይጠበቅበታል። እንዲሁም ተጫራቾች በዋናው ፖስታም ሆነ በውስጥ ሰነዶች ውስጥ የመረጡትን LOT በግልፅ መጻፍ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ለመውሰድ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ጨረታ ቁጥር (SSNT-T-586) በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜል ያገኛሉ ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብና ቅድመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  6. አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል የመጫረቻ ሠነዳቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 09:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት ግቢ ውስጥ የቀድሞ የሰው ሀብት አስተዳደር ህንፃ በጨረታ መክፈቻ ክፍል በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:15 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ወ/ ሮ ሰላማዊት አባተ

ስልክ ቁጥር፡ 011-517-42-58

ኢ-ሜይል: selamawita@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender