Tender Detail

Tender Details

  • Company The Brooke Hospital for Animals. (ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ)
  • Address 22 ማዞሪያ በአውራሪስ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ ባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ በንጋት ህንፃ እና በአዳነ ገብሩ ህንፃ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-661-00-69
  • Websitehttps://www.thebrooke.org/
  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600.00
  • Bid Securityከጠቅላላው የጨረታ ዋጋቸው 2%
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories Water Construction

ዘ ብሩከ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በዚህ ዓመት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ነገሌ አርሲ ወረዳ ለሚሰራው የነገሌ አርሲ የተቀናጀ የጋማ እንስሳት እንክብካቤ ማዕከል አገልግሎት የሚውል ውሃ ለማስገባት ይፈልጋል፡፡

The Brooke Hospital for Animals. (ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ዘ ብሩከ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በቁጥር፡ 0883 የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ዋና ቢሮውን አዲስ አበባ -በማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የድርጅቱ አላማ የጋማ እንስሳትን ደህንነትና ጤንነት ማሻሻል እና በእነዚህ የጋማ እንስሳት ጉልበት ኑሯቸውን የመሰረቱ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ሲሆን ይህንንም ለመተግበር ከመንግስት የእንስሳት እና የግብርና ተቋማት ጋር በትብብር ይሠራል፡፡ ድርጅታችን በዚህ ዓመት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ነገሌ አርሲ ወረዳ ለሚሰራው የነገሌ አርሲ የተቀናጀ የጋማ እንስሳት እንክብካቤ ማዕከል አገልግሎት የሚውል ውሃ ለማስገባት ይፈልጋል፡፡

ይህንንም ለማድረግ ድርጅታችን ብሩክ ኢትዮጵያ ብቁ እና መስፈርቶችን የሚያሟሉ ደረጃ ስድስት የውሃ ስራ ተቋራጭ (WWC Six and above) የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎኘ በማቅረብ እንድትወዳዳሩ ይጋብዛል፡-

 

የጨረታ ቁጥር

የፕሮጀክቱ ስም

ወረዳ/ከተማ

የሥራው አይነት

የውኃ ሥራ ለነገሌ አርሲ የጋማ እንስሳት እንክብካቤ ማዕከል

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ነገሌ አርሲ ወረዳ

B-ETH/17/2025

NEGELE ARSI

INTEGRATED ANIMAL WELFARE & HEALTH TRAIN-ING CENTER PIPE LINE EXTENSION

WWC-Six and ABOVE

Cattle Trough, Water Point and Pipe Line etc

 

    1. ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ ማስረጃችሁን የጨረታ ሰነድ ስትገዘ ማቅረብ ይጠበቅባችሗል፡፡
    2. ተጫራቾች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 797 ከሚገኘው የድርጅታችን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር (600.00 መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
    3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋቸው 2% ቦንድ በሲፒኦ መልክ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሲፒአው የጨረታ ኤንቨሎፕ ውስጥ ለብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡ የቀረበው ሲፒኦ ከሃሳብ ስሌት ማስተካከያ በኋላ ለሚመጣው ጠቅላላ ዋጋ የ2% ከ20% በታች ከሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
    4. ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ለቅድመ ክፍያ የሚሆን የሁኔታዎች ያልተወሰነ /Unconditional Bank Guar antee/ የባንክ ዋስትና 30% ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
    5. ተጫራቾች የታሸገውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ከላይ በተቁ 2 በተጠቀሰው አድራሻ በሚገኘው የብሩክ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ሲሆን። የጨረታ ማቅረቢያው 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ፣ ወይም በበዓል ቀናት ከዋለ የጨረታ መዝጊያው ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይሆናል ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
    6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን በተ.ቁ. 5 የተመለከተው ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
    7. ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጨረታ መክፈቻውን ቀን የማራዘም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ቀደም ብሎ በድርጅቱ ሥራዎች ላይ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የጨረታ ተወዳዳሪዎች ከጨረታው እንዳይሳተፉ ማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።
    8. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-661-0069/011-662-1885 በመደወል ወይም በኢሜይል info@thebrookeethiopia.org አድራሻችን መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻችን፣ 22 ማዞሪያ በአውራሪስ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ ባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ በንጋት ህንፃ እና በአዳነ ገብሩ ህንፃ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ነው፡፡ ስልክ ቁጥር 011-661-0069/011-662-1885

 

ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ

 

Save Tender