Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security250,000 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-15 00:00:00
  • Categories Water Pipes And Fittings

ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ለ ለዙሀሙሲት፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እና ለገዳ እያሱ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል የዕቃ አቅርቦት ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ግዥ ፈፃሚው አካል ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን

ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር NCB WWCO5/2018

 

ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ለ ለዙሀሙሲት፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እና ለገዳ እያሱ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል የዕቃ አቅርቦት ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ

የሎት ቁጥር

ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር/ ዓይነት Summary of goods

መለኪያ

ብዛት

ምርመራ

1

 

ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ

በአይነት

183

 

 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. የዘመኑን ግብር ከፍለዉ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፤ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባዉ ፈርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ 60 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ 250,000 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ. አ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ኮርፖሬሽን ዋናው መስሪያ ቤት ከገንዘብ ያዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ ከሚገኘው አ.አ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ነጋ ቦንገር ሆቴል 100ሜ ገባ ብሎ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን (የዋጋ ሰነዳቸውን) በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ከተማ በውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ በግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 20 ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በ ግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰነድ ግዥ መፈፀም እንጅ ፖስታውን ማስገባት የሚቻለው ባህር ዳር ከተማ ዋናው መስሪያ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ: - የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን መስሪያ ቤት

ዳግማዊ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት ፖ.ሣ.ቁ 106, ስልክ ቁጥር 0582221479, ባህር ዳር

 

ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender