የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለወጣት ማዕከሎች የሚውል የተለያዩ የቢሮና የመዝናኛ እቃዎችን ለመግዛት ህጋዊ ሆ እና በዘርፉ የተሠማሩ የንግድ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማጫረት ይፈልጋል በመሆንም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2018
የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለወጣት ማዕከሎች የሚውል የተለያዩ የቢሮና የመዝናኛ እቃዎችን ለመግዛት ህጋዊ ሆ እና በዘርፉ የተሠማሩ የንግድ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማጫረት ይፈልጋል በመሆንም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
10) ተፈላጊው መስፈርት እንደሚመለከተው ይሆናል፡፡
1. የቫት ተማጋቢ መሆኑን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያለው ኮፒውን ማቅረብ የሚችል፡፡
2. በሥራው መስክ በዘርፉ የተሠማሩና የታደሰ የንግድ ፍቃድና ምዝገባ ያለው፡፡
3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበና የምዝገባ ሰርትፊኬት ያለው፡፡
4. ናሙና ከአቅራቢው ድርጅት ሲሆን የዕታው ዓይነት (ስፔሲፊኬሽን) በጨረታው ሰነድ ላይ ግልፅ ይሆናል፡፡
5. ሰነዱን ማግኘት የሚቻለው የማይመለስ የኢት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ዋጋ በመከፈል ነው።
6. ሰነዱን ማግኘት የሚቻለው ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2:30 - 6:30 ከሰዓት በላይ ከ8:00-11:00 ከኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ከፍል ቢሮ ቁጥር 19 በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ከጠቅላላ የግዥ ዋጋ 1% ሲፒኦ (CPO) ከታወቀ ባንክ በኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስም አሰርቶ ማምጣት የሚችል፡፡
8. ጨረታውን ካሸነፈ ውል ማስከበሪያው ከጠቅላላ ግዥው ገንዘብ መጠን ልክ 10% ሲፒኦ (CPO) ከታወቀ ባንከ አሰርቶ ማምጣት የሚችል፡፡
9. የተወዳዳሪዎች ፖስታ፤ አድራሻ፣ ፊርማ፣ የድርጅቱ ማህተም እና ስልከ ቁጥር መኖር፣ እንዲሁም በሠም መታሸግ አለበት።
10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. የማወዳደሪያ ቦታ በኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ውስጥ ይሆናል፡፡
12. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን አሸንፎ ውል ከተቀበለ እና ውል ገብቶ ዕቃውን ካላስረከበ የጨረታው ወይም የውሉ ማስያዣ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
13. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱ ተሽጦ በ 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡
14. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪው በአካልም ሆነ ህጋዊ ወኪል መላከ ይችላል፡፡ ሆኖም የተወዳዳሪው አለመገኘት የጨረታውን መከፈት እያደናቅፍም።
15. አሸናፊ ድርጅቶች ዕቃውን ጭነው ቢሮው በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ማስረከብ አለባቸው::
16. የቴክኒክ እና የፋይናንሺያል ዶክሜንት ኦሪጂናል እና ኮፒ ለየብቻ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ሲፒኦ የፋይናንሺያል ዶክሜንት ውስጥ መግባት አለበት፡፡
17. ከላይ የተቀመጠው የጨረታው መከፈቻ ቀን በበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ ወደሚቀጥለው ቀን የሚዛወር ይሆናል፡፡
ለ) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-66-30-88/0911067339 በመደወል መረዳት ይቻላል፡፡
አድራሻ:- ቂርቆስ ከፍለ ከተማ ጠመንጃ ያዥ ሰፈር ከኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ድርጅት ዋና መ/ቤት ጎን (ጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንከ) ፊት ለፊት፡፡
የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ፊንፊኔ /አዲስ አበባ
