በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሠራቸው የግንባታ ሥራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ቂ/ክ/ከ/ዲ/ግ/ስ/ጽ/ቤ/ት 001/18
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሠራቸው የግንባታ ሥራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለሥራው አሥፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሸነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ሥራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
|
ተራ ቁጥር/ ሎት |
የፕሮጀክት ስም |
የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታ ዋስትና ብር መጠን |
የተቋራጭ ደረጃ |
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
|
1 |
ብሄራዊ የመጀመሪያና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት ጂ+2 ግንባታ |
ወረዳ 9 |
200 ሺህ |
GC 6 ደረጃ ኮንትራክተር እና ከዚያ በላይ |
60 |
|
2 |
ወረዳ 9 የህጻናት ማቆያ ማጫወቻ ጂ+0 ግንባታ ሥራ |
ወረዳ 9 |
100 ሺህ |
BC 7 ደረጃ ኮንትራክተር እና ከዚያ በላይ |
60 |
|
3 |
ወርሃ የካቲት ቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ጂ+2 ግንባታ |
ወረዳ 4 |
200 ሺህ |
GC 6 ደረጃ ኮንትራክተር እና ከዚያ በላይ |
60 |
|
4 |
ህይወት አምባ ጤና ጣቢያ ጂ+4 እድሳት |
ወረዳ 5 |
100 ሺህ |
GC 7 BC 6 ደረጃ ኮንትራክተር እና ከዚያ በላይ |
60 |
|
5 |
ህይወት አምባ ጤና ጣቢያ ጂ+4 እድሳት (ሱፐርቪዥን) |
ወረዳ 5 |
50 ሺህ |
ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ አማካሪ |
60 |
|
6 |
ወርሃ የካቲት ቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ጂ+2 (ሱፐርቪዥን) |
ወረዳ 4 |
50 ሺህ |
ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ አማካሪ |
60 |
|
7 |
ብሄራዊ የመጀመሪያና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት ጂ+2 (ሱፐርቪዥን) |
ወረዳ 9 |
50 ሺህ |
ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ አማካሪ |
60 |
|
8 |
ወረዳ 9 የህጻናት ማቆያ ማጫወቻ ስራ (ሱፐርቪዥን) |
ወረዳ 9 |
ዋስትና ደብዳቤ |
ኮ/ዘ/ጥ/አ/ ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 እና 11 ኢንተርፕራይዝ |
60 |
- ለሥራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር (2017 ዓ.ም የከፈሉ፣ የታደስ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list)፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ፤ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፤ ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል)።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት (Calendar Days) የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር በሥራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት በምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ወለል በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱት ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው የመቁጠሪያ ቀን (Calendar Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 22ኛው የሥራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን 4 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለ 90 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE/ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሠራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጣነ (unbalanced Bid) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- በሥራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ሥራውን በነጻ እንደሚሠራ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያን በሚያዘው መሠረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በክፍለ ከተማው በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል ፡፡
አድራሻ ፡- ማሪዮት ሆቴል ጎን በስተምስራቅ በሚገኘው ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት 5ተኛ ፎቅ በምህንድስና ግዢ ቡድን መሆኑን እንገልጻለን።
ስልክ ቁጥር 0115-58-44-25
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት
