በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገ/ት የሚውል የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገ/ት የሚውል የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ /Tin/ ሰርተፍኬት ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግን/አስ/ር ዳይት ቢሮ በኢ/ያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር 1000510994577 በማስገባት የጨረታ ሰነዱን መወሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የመንግስት ስራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ አገ/ት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
- 16ኛው ቀን የመንግስት ስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግስት ስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በራሱ ወጪ የዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ በሚገኘው የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ 0475562232 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
