Tender Detail

Tender Details

  • Company የሸገር ከተማ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ተቋም
  • Address በልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጎን የጨፌ አነኒ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912074844
  • Website
  • Deadline10 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityለማሽነሪ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና ለመኪና ኪራይ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-10 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent , Machinery

የሸገር ከተማ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ተቋም የሚከተሉትን መስፈርት እና ህጋዊ ሰውነት ያላቸውን አካላት በግልጽ ጨረታ ለውድድር በማሳተፍ ለተለያዩ መ/ቤቶች የመኪና ኪራይ እና ለሸገር ከተማ ልማት የማሸነሪዎች ኪራይ ላይ በሸገር ከተማ ውስጥ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የሸገር ከተማ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ተቋም


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሸገር ከተማ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ተቋም የሚከተሉትን መስፈርት እና ህጋዊ ሰውነት ያላቸውን አካላት በግልጽ ጨረታ ለውድድር በማሳተፍ ለተለያዩ መ/ቤቶች የመኪና ኪራይ እና ለሸገር ከተማ ልማት የማሸነሪዎች ኪራይ ላይ በሸገር ከተማ ውስጥ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ መስፈርት

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የታክስ መለያ ቁጥር (TIN NO) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት
  2. አዲስ አበባ ወይም ሸገር ከተማ ውስጥ የሚሰራበት ቢሮ ያለው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የድርጅቱን ፕሮፋይል ማቅረብ የሚችል
  3. በዘርፉ (የመኪና ኪራይ ላይ) እንዲሁም (የማሽነሪዎች ኪራይ ላይ) በአቅራቢነት ላይ ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ ልምድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ የሚሽነሪ ኪራይም ሆነ የመኪና ኪራይ ለየብቻቸው ውድድር የሚደረግባቸው መሆኑን አውቆ መሳተፍ የሚችል፤
  4. ተጫራቾቹ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ የመኪና አከራዮች በመኪና ላይ እንዲሁም የማሽነሪ አከራዮች ደግሞ በማሽነሪ ኪራይ ላይ መሆን ይኖርባቸዋል፤
  5. ማሽነሪዎችንም ሆነ መኪናዎችን በተጠየቀው ሞዴል እና የመጫን አቅማቸው ማቅረብ የሚችል፤
  6. በቴክኒክ ደህንነታቸውን የጠበቁ ማሸነሪ እና መኪናዎችን ማቅረብ የሚችል፤
  7. ጨረታውን ካሸነፈ እና በውል ውስጥ በሚጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ የሚችል እና ካቀረበም በኋላ ማንኛውም እክል ወይም ችግር ካለበት በገዥው አካል የሚሰጠውን ሀሳብ በመውሰድ ጤናማ ማሽነሪ እና መኪናዎችን ማቅረብ የሚችል፤
  8. ለጨረታ ማስከበሪያ (ዋስትና) ለማሽነሪ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና ለመኪና ኪራይ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ሲፒኦ (C.P.O) Unconditional Bank Guaranty በሀገሪቱ ከታወቀ ባንከ ማቅረብ የሚችል፡፡
  9. በእያንዳንዱ የፋይናንስ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሥራ አስኪያጅ ወይም ድርጅቱ/ተቋሙ በወከለው ህጋዊ ወኪል ፍርማ እና በድርጅቱ በተቋሙ ማህተም ተረጋግጦ መቅረብ አለበት፤
  10. ተጫራቾች በድርጅታቸው ስር የሚተዳደሩ ቋሚ ሠራተኞችን ዝርዝር ከነ የሥራ ድርሻቸው በተመሰከረለት በውጪ ኦዲተር የተሰራን ሪፖርት ኮፒ ማቅረብ የሚችል
  11. አመታዊ የገንዘብ እንቅስቃሴን (Transaction) በተመሰከረለት የውጪ ኦዲተር ሪፖርት ማቅረብ የሚችል፣
  12. የፋይናንስ ኦርጂናል እና ኮፒ እንዲሁም የቴክኒክ መረጃዎችን ኦርጆናል እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ የሚችል፤
  13. የዚህ ጨረታ ሰነድ በቀን 16/03/2018 ጀምሮ እስከ 30/03/2018 ድረስ በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ01/04/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  14. በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ከሸገር ከተማ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ተቋም ከፋይናንስ ግዥ እና የንብረት አስተዳደር በአካል ቀርበው በማይመለስ 1000 ብር (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መወዳደር ትችላላችሁ።

 

አድራሻ ፡- በልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጎን የጨፌ አነኒ ህንፃ አንደኛ ፎቅ

ለተጨማሪ መረጃ 0912074844

 

የሸገር ከተማ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ

 

Save Tender