Tender Detail

Tender Details

  • Company በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ (Sidama National Regional Government Livestock Development Office)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ሲዳማ ብ/ክ/መ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916108360
  • Website
  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security30,000.00
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Others , Electronics Materials

የጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 03/2018 ዓ.ም የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል (ለ2ኛ ጊዜ) ፣የኤለክትሮንከስ ዕቃ (ለ2ኛ ጊዜ) እና የሐር ልማት ቁሳቁስ (ለ2ኛ ጊዜ) ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ (Sidama National Regional Government Livestock Development Office)


የጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 03/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል (ለ2ኛ ጊዜ) ፣የኤለክትሮንከስ ዕቃ (ለ2ኛ ጊዜ) እና የሐር ልማት ቁሳቁስ (ለ2ኛ ጊዜ) ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-

1) በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ተጨማሪ ዕሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣ጨረታ መሳተፍ የሚችልና የምዝገባ ምስከር ወርቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል፡፡

2) ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15(አስራ አምስት ቀን) ተከታታይ ቀናት የጨረታ ዶከመንት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ባንከ በማስገባት ከመ/ቤቱ ግዥ ኬዝ ቲም ከጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ሲዳማ ብ/ክ/መ/እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 በአካል ሆነ በተወካዮቻቸው አማካይነት መግዛት ይቻላል።

3) በየዘርፉ የጨረታ ማስከበሪያ(Bld Bord) ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና/Bank GAURANT/ወ ይ ም የ ከ ፍ ያ ማዘዣ (CPO) ከመጨረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ጨረታ ማስከበሪያ ከቴከኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት ::

4) አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፡፡

5) ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴከኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል)እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን (ተከታታይ ቀናት) ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ኬዝ ቲም ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡በአስራ ስድስተኛው ቀን ሰነድ መሸጥና መግዛት አይቻልም፡፡

6) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል፡፡የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም፡፡

7) መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

8) መ/ቤቱ ሚያዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅት ህጋዊ ማህተም ሳያደርግ የቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ዉጪ ይሆናል፡፡

9) የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይበተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

10) የሰነድ ማስገቢያ ከመጨረሻው ቀንና ሰዓት በኃላ የሚመጡ አመልካቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

11)ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916108360/0916070057 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ - ከጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 እንገኛለን፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ

Save Tender