Tender Detail

Tender Details

  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጿል
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories Safety And Security , Mechanical Work and Materials

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት የኤል ኢ ዲ ቢል ቦርድ ገጠማ አገልግሎት እና የእሳት አደጋ ማጥፊያ አገልግሎት ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 006/18

 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት የኤል ኢ ዲ ቢል ቦርድ ገጠማ አገልግሎት እና የእሳት አደጋ ማጥፊያ አገልግሎት ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ክሊራንስ ወይም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል ከፍለው ደረሰኝ ይዘው ከአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 208 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል/ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ አሽጎ አርጅናልና ኮፒ በማለት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን የብር መጠን በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋሰትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከ8፡30 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  7. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ስልክ ቁጥር +251-11-6-45-41-47/11-6-45-35-98/11-8-69-49-31 ከመገናኛ አያት መንገድ ከሰዓሲተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ዋና በር ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ ነው።

 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

 

Save Tender