በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በ2018ዓ.ም በጀት አመት ለሞላሌ ከተማ አስተዳደሩ የቢሮ አጥር እና የጥበቃ ቤት/ማማ ግንባታ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አውጥቶ ግንባታውን ማስገንባት ይፈልጋል።
የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት /ሞላሌ/
የጨረታ ቁጥር ጨ/ቁ 002/2018
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በ2018ዓ.ም በጀት አመት ለሞላሌ ከተማ አስተዳደሩ ማለትም
ሎት 1- የቢሮ አጥር እና የጥበቃ ቤት/ማማ ግንባታ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አውጥቶ ግንባታውን ማስገንባት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት-
- በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው
- የግንባታው የገንዘብ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱት እና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሚገነባው ለቢሮ አጥር እና ለጥበቃ ቤት/ ማማ ግንባታ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችሉት ኮንትራከተሮች ወይም ኢንተርፕራይዞች ከደረጃ 8 /ስምንት/ እና በላይ ህንፃ ስራ ተቋራጭ /B.C/ እና ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ/G.C/ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- የሚገነባው የቢሮ አጥር እና የጥቢቃ ቤት ማማ ግንባታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ አርቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኋላ በሚገኘዉ ጠቅላላ ድምር 2% በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንኮች በሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር አፊ ክሬዲት /CPO/ እና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የግንባታ ቢን ኦፍ ኳንቲቲው ውስጥ የተዘረዘሩትን የግንባታ ዓይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ስልክ ቁጥር ፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የተጫረተበትን የቢሮ አጥር እና የጥበቃ ቤት ማማ ግንባታ የጨረታ ሰነድ አንድ ወጥ በሆነ አንድ ፖስታ ብቻ ማለትም እንድ ኦርጅናል በጥንቃቄ ታሽጎ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደርቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ22 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ። በእዚሁ እለት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ጨረታው በይፋ ይከፈታል።
- ይህ የግንባታው ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መግዣ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ሌሎች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ያልተካተቱ ወይም ያልተገለፁ ካሉ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ እና በአዋጁ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-622-07-79 ደውለው ይጠይቁ።
የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት
ሞላሌ
