በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት መሳሪያዎች፣የፅዳት እቃ፣የቢሮ መሳሪያዎች፣ የህትመት፣ የደንብ ልብስ፣የጥገና እቃዎች፣ የእስፓርት እቃዎች እና ሌሎች አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 አዲስ አምባ አፀደ ህፃናት የመ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት መሳሪያዎች፣የፅዳት እቃ፣የቢሮ መሳሪያዎች፣ የህትመት፣ የደንብ ልብስ፣የጥገና እቃዎች፣ የእስፓርት እቃዎች እና ሌሎች አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ ጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
1. እቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ብቃት፤ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስከር ወረቀት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
3. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ VAT፣ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም የተመዘገቡበትን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ብር 10000 (አስር ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ ሰነድ (C.P.O) ከጨረታው ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመከፈል ሰነዱን ከአዲስ አምባ የመ/ደ/ት/ቤት/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ክፍል ቀርበው በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች በገዙበት የጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ ዝርዝር መሙያ ላይ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡በሌላ ሰነድ ላይ ከሞሉ ተቀባይነት የለውም ፡፡
8. ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት(VAT)ማካተት አለባቸው፡፡
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 1ዐ ኛው የሥራ ቀን አየር ላይ ውሎ በ 10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም በተቀመጠው ጊዜ እና ስዓት ይካሄዳል፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ ዋጋ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ዉስጥ አድርገው ማቅረብ አለባቸው ።
1. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ደብዳቤ ይዘው የሚመጡ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ ሲያመጡ የተደራጁበትን ዘርፍ ተጠቅሶ ቀጥታ በት/ቤቱ ስም ማፃፍ አለባቸው ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሰነዱን መግዣ ዋጋ እና የውል ማስከበሪያ በነፃ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቅሶ መፃፍ አለበት።
12, ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አዲስ ሰፈር ድልድይ ወረድ ብሎ አዲስ ሰፈር ጣና ገበያ ፊትለፊት፡፡
ስተጨማሪ መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 011-42-04- 41 / 011-470-70-17 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት
