በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት በከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው የተለያዩ ከዚህ በታች በሎት በተቀመጡ የግንባታ ሥራዎች በተቋሙ ባለው በጀት ማሠራት ይፈልጋል።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት በከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት በከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው የተለያዩ ከዚህ በታች በሎት በተቀመጡ የግንባታ ሥራዎች በተቋሙ ባለው በጀት ማሠራት ይፈልጋል።
ሀ በሎት 01፡ ዳኸራ/ ካምቦ እና ወዲፋ መንድር/፣ያጋ፣ አጋሮ/፣ አይዳ ባጫ፣ እና የዳ ኮጵሽ 16 ምንጭ ውሃ ግንባታ
ለ በሎት 02፡ ቢጋ፣እራሞ፣ ኦላ፣መቻ ቀበሌዎች 4 ምንጭ ውሃ ግንባታ/፣
ሒ በሎት 03፡ ኦማ ሾንጋ፣ጊዳ፣ኡፋ ገነት፣ጎፓ/4 ምንጭ ውሃ ግንባታ/፣
መ. በሎትo4፡ የቡታ ሆራ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የቄራ አገልግሎት መስጫ ግንባታ፣
በአጠቃላይ ከላይ ከተራ ቁጥር ሀ-ሐ ድረስ በተቀመጡ ቀበሌዎች የውሃ ምንጭ ግንባታ ሥራ በተራ ቁጥር መ ደግሞ የቄራ አግልግሎት መስጫ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ከደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የሆነ (የውሃ ግንባታWWC/ ብቃት ማረጋገጫ ለውሃ ግንባታ ለቄራ ደግሞ ጠቅላላ ግንባታ ሥራ) ብቃት ማረጋገጫ ያላቸውን ድርጅቶች ወይም ማኅበራት አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባችኋል
1. የዘመኑ የታደሰ ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ ያለው፣
2 የዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
3 የቫት/ቲኦቲ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
4. ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል /ለማኀበራት ብቻ)፣
5 የአቅራቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችል፣
6. የንግድ ምዝገባ እና ቲን ነምበር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
7 አንድ ግንባታ ድርጅት መወዳደር የሚችለው በአንድ ሎት ብቻ ሆኖ በተጨማሪ መወዳደር ከተፈለገ በሎት አራት ላይ ብቻ በተጨማሪነት መወዳደር ይችላል፡፡
8. ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ በውሃ ግንባታ ሥራ የሥራ ልምድ እና መልካም አፈጻጸም ማስረጃ ከህጋዊ ተቋም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
9. በወረዳው ውስጥ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ አሸንፎ ሥራውን በማስተጓጎልም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸውን ድርጅቶች ወይም ማኀበራትን ጨረታው አያሳትፍም፣
10. ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነድ ሁለት ሁለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ለሎት 01 ብር የ35000/ሰላሳ አምስት ሺህ ብር፣ ለሎት 2 እና ፡ ለሎት 03 ብር የ25000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ለሎት 04 ብር የ30000/ሰላሳ ሺህ ብር / CPO በሺሾ እንዴ ወረደ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሠርተው ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በአማራጭነት ከተፈለገ በካሽ አደርገው በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ሥም ባለው የንግድ ባንክ ሂግብ ቁጥር 1000261080808 ላይ ገቢ በማድረግ የባንኩን ስሊፕ ማስያዝ ይችላሉ::
12. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ጨረታው ከፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ ብቻ እየከፈሉ ከሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 5ት ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
13. ጨረታው በ22ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰአት ተጫራቾች / ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በታሽገበት ዕለት ከሰዓቱ በ8፡00 ሰአት ተጫራቾች/
ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
14. ተጫረቶች ህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሰነድ የመክፈት ሂደቱን
አያስተጓጉልም፡፡
15. የጨረታ መዝግያና መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይሰዓት ይሆናል፡፡ 2
ማሳሰቢያ መ/ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0476680200 መጠየቅ ይችላሉ።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት በከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ ቤት
