የሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለሮቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል Smart Pole Street lighting installation ስራ ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለሮቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል Smart Pole Street lighting installation ስራ ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በ Electro mechanical ፍቃድ ያለው በደረጃ አምስት /5/Gር እና ከዛ በላይ ፍቃድ ያላችሁ ድርጅቶች ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበት ተጓዳኝ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና ክሊራንስ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በተሰማሩበት ስራ ዘርፍ / EGp Supplier List/ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ቴክኒካል must meet ኦርጅናል ሰነዶችን በእጃቸው ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራች ቴክኒካል ኦርጅናልና ሲፒኦ በተለያየ ፖስታ ለየብቻ ከታሸገ በአንድ ፖስታ ማሸግ ይኖርበታል ፖስታ ላይ ቴክኒካል ኦርጅናል ዶከመንት የሚል ጹሁፍ ሊኖረው ይገባል። ሁለት ቴክኒካል ኮፒ ለየብቻ ከታሸገ በኋላ በአንድ ፖስታ ማሸግ ይኖርበታል። ፖስታው ላይ ቴክኒካል ኮፒ ዶክመንት የሚል ጹሁፍ ሊኖረው ይገባል። ሁሉንም ዶክመንት በአንድ ትልቅ ፖስታ ከታሸገ በኋላ ፖስታው ላይ ቴከኒካል እና ሲፒኦ ከሙሉ መረጃ ጋር ማቅረብ አለበት፣
- ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል በተለያየ ሁለት ፖስታ መታሸግ አለበት፤ እንዲሁም ፖስታው ላይ አርጅናል ፋይናንሻል ዶክመንት እና ኮፒ ፋይናንሻል ዶከመንት ጽሁፍ ሊኖራቸው ይገባል፤ ሁሉንም ዶክመንት በአንድ ፖስታ ከታሸገ በኋላ ፋይናንሻል ዶክመንት የሚል ጽሁፍ ሊኖረው ይገባል።
- ከላይ ተራ ቁጥር 5 እና 6 የተጠቀሱት ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል። ፖስታው ላይ የጨረታው ቦታ አድራሻ እንድሁም BID Submission sheet የተጠቀሱ መረጃ ሊይዝ ይገባል፤
- የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ ይደረጋል።
- አሸናፈው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ መ/ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በዲዛይን እና እስፔስፍኬሽን መሰረት የስማርትና ብላክ ፖል ለየብቻ ናሙና ማቅረብ አለበት ካላቀረበ ውድቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ ከሮቤ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን በመግዛት እና ሰነዱን ከሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ ።
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ22 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጋልማ ኣባ ገዳ አዳራሽ ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0226650145 ደውለው ይጠይቁ።
የሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
