ተቋማችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተሽከርካሪ ጥገናና ትራንስፖርት አስተዳደር ስር ለሚገኙ የተቋሙ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተሸከርካሪ ዘይት፣ ማለስለሻ ቅባት እና ግሪስ በማሕቀፍ ስምምነት ግዥ (ግልጽ ጨረታ) አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ፍፋግ/ግጨ-012/2018
ተቋማችን ለተሽከርካሪ ጥገናና ትራንስፖርት አስተዳደር ስር ለሚገኙ የተቋሙ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተሸከርካሪ ዘይት፣ ማለስለሻ ቅባት እና ግሪስ በማሕቀፍ ስምምነት ግዥ (ግልጽ ጨረታ) አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው/አገልግሎት ዓይነት |
ግምታዊ የአንድ ዓመት የፍላጎት መጠን |
መለኪያ |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
Engine Oil 15W-40 |
14,000 |
ሊትር |
500,000.00 (አምስት መቶ ሺ ብር) |
ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
|
2 |
Engine Oil – 10W-30 |
11,000 |
ሊትር |
|||
|
3 |
Differential Oil SAE 90 (Light-duty) |
800 |
ሊትር |
|||
|
4 |
Differential Oil SAE 140 (Heavy-duty) |
600 |
ሊትር |
|||
|
5 |
Hydraulic Oil SAE 10 |
1,500 |
ሊትር |
|||
|
6 |
Brake Fluid DOT 4 |
100 |
ሊትር |
|||
|
7 |
Grease for Bearings |
1,000 |
ኪ.ግ |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መሥሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መሥሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መሥሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል ስልክ ቁጥር 011-126-66-05/011-156-01-48
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና "Ethiopian Electric Utility" በሚል መሆን ይኖርበታል፤
- የማሕቀፍ ስምምነት ግዥው ፀንቶ የሚቆየው ለ3 (ሦስት) ዓመት ነው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
