Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ሸኮ ዞን በሲዝ/ከ/ስስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በማችንግ ፈንድ በተገኘ በጀት የቴራዞ ንጣፍ እና ግሪነሪ ማልማት ሥራ ብቁ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ሸኮ ዞን በሲዝ/ከ/ስስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በማችንግ ፈንድ በተገኘ በጀት የቴራዞ ንጣፍ እና ግሪነሪ ማልማት ሥራ ብቁ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ GC/RC- ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፤ የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት፤ በአቅራቢዎች ሰም ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች በጽ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ብር ብቻ በመክፈል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀን /አስራ አምስት ቀን/ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30-6:30 እና 7:30-11:30 ሰዓት ድረስ ከጽ/ቤቱ ግዥ ፋ/ን) አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በሲፒኦ በሲዝ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም አሠርተው ለብቻ በአንድ ፖስታ በማሸግ በቴክኒካል ማስረጃ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው ስለሚከፈት የጨረታ አከፋፈቱን ሥነ-ሥርዓት መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሲዝ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  5. የግንባታው የሳይት ቦታ በሲዝ ከተማ አስ/ር በከተማው መሐል ሠፈር በሚገኘው በመስቀል አደባባይ ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን ተጫራቹ በራሱ ወጪ ሳይቱን በመመልከት ከሲዝ/ከ/አስ/ር/ማ/ቤ/አ/ሎት/ጽ/ቤት የምልከታ ደብዳቤ ማቅረብና ሰነድ ውስጥ ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. የግንባታው የማጠናቀቂያ ጊዜ የውል ስምምነት ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ በ60 ቀናት ውስጥ ይሆናል።
  7. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ40 ቀናት ብቻ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
  9. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የግንባታ ሥራው የመወዳደሪያ ሃሳብ ደጋፊ ሰነዶች በግልጽና በጥራት መግለጽ አለባቸው። ይህም የሚሆነው ከላይ በተገለጸው የግዥ መለያ ቁጥር መሠረት ሆኖ ከተገለጹት ጉዳዮችና ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመና ተቀባይነት ያላቸው መሆን አለባቸው።
  10. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሃሳብ እና ሌሎችም ተጨማሪ ማረጋገጫዎች የሚመለከተው ኃላፊ ፊርማና ማኅተም ካልተደረገባቸው የቀረበ የመወዳደሪያ ሃሳብ ሊሰረዝ ይችላል።
  11. ጽ/ቤታችን የዚህን ግንባታ ግዥ የሚፈጽመው የተዘረዘሩትን ሁኔታዎችና ቴክኒካል መመዘኛዎች ከሚያሟሉት መካከል በመንግሥት በግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ዝቀተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች የግዥ ትዕዛዝ በመስጠት ይሆናል።
  12. አሸናፊ ተጫራቾች የውሉን 10 ፐርሰንት የውል አፈጻጸም ዋስትና በተጨማሪ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  13. አሽናፊ ተጫራች የውሉን 30 ፐርሰንት የቅድመ ክፍያ ሲጠይቅ ተመጣጣኝ የባንክ ጋራንቲ ሲያቀርብ የሚከፈል ይሆናል፡፡
  14. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. በጨረታው ላይ ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች በጽ/ቤቱ አድራሻ በኩል ምላሽ ማግኘት ይቻላል፡፡
  16. የጽ/ቤቱ አድራሻ በሲዝ/ከ/አስ/ር ፋ/ኢኮ/ጽ/ቤት ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ 0477770620

0911452713 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ

 

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/በቤንች ሸኮ ዞን የሲዝ ከተማ አስር ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት/ሲዝ/

 

Save Tender