የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የህትመት፤ የምግብ ቤት ዕቃዎችና ላውንደሪ ማሽን፤የአንቲ ቫይረስ እና የፈርኒቸር ግዥ የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 005/18
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የህትመት፤ የምግብ ቤት ዕቃዎችና ላውንደሪ ማሽን፤የአንቲ ቫይረስ እና የፈርኒቸር ግዥ የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት
አለባቸው፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. ተጫራቾች በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታከስ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይበሥራ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመከፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ /የጨረታ ሰነድ ላይ/ የተገለፀውን ብርበሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ይህ የጨረታ ደብዳቤ ወጪ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
6. የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
7. ተጋብዘው ፍቃደኛ በመሆን ሰነድ የመለሱ ድርጅቶች በተሰጣቸው ናሙና መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት
