የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ጠጠር (Coarse Aggregate 2mm) እና አሸዋ (River Sand) በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/PMO/NCB/07/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ጠጠር (Coarse Aggregate 2mm) እና አሸዋ (River Sand) በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 175,000.00 (አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በእ.ኤ.አ. ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ወይም EU-PMO ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጨረታ ቁጥር EEU/ PPM/NCB/08/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በእ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ማህበራዊ ዋስትና ህንጻ ላይ ከ11ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከ ሰዓት 7፡00 –11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00 – 6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-126-3153 መደወል ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
