Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Administration Public Procurement and Property Disposal Service
  • Address Mexico Sengatera, behind St. Mary University College., located at Yobek Commercial center., Phone: 0118-26-62-35
  • Website
  • Deadline05 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600.00
  • Bid Security100,000.00
  • opening date2025-12-05 00:00:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Vehicle , Vehicle Spare Parts

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፥ በስከራጥ (በቁርጥራጭ) መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርየውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የሆኑ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ የተፈታቱ የክሬሸርአካላት ባሉበት፣ በርሜሎች፣ አስፋልት ፕላንት ጀኔረተሮች፡ ሌሎችም) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Addis Ababa City Administration Public Procurement and Property Disposal Service


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፥ በስከራጥ (በቁርጥራጭ) መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርየውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የሆኑ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ የተፈታቱ የክሬሸርአካላት ባሉበት፣ በርሜሎች፣ አስፋልት ፕላንት ጀኔረተሮች፡ ሌሎችም) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ህዳር 9/2018 ጀምሮ ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ፕላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት የተለያዩ የአገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ 600.00 (ስድስት መቶ ብር)፣ የተለያዩ ያገለገሉ የንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ የተፈታቱ የከሬሸር አካላት ባሉበት፣ በርሜሎች፣ አስፋልት ፕላንት፣ ጀኔረተሮች፣ እና ሌሎችም) ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) እንዲሁም የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ቶነር ካርትሌጅ ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ 300.00 (ሶስት መቶ ብር)፣ በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ።

2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቾች ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ ።

3. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልገሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል።

4. ተጫራቾች ትከከለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው።

5. ተጫራቶች በአንድ መለያ ቁጥር(መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው።

6. ተጫራቾች ለሸያጭ የተዘጋጁትን ተሽከርካሪዎች፣ /በስከራፕ/ በቁርጥራጭመልከ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የሆኑ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርየተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ ንብረቶች /የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣የተፈታቱ የክሬሸር አካላት ባለበት፣ በርሜሎች፣ አስፋልት ኘላንት፣ ጀኔረተሮች፣ እና ሌሎችም የአንዱን መስሪያ ቤት በጥቅል መጫረት አለባቸው:

7. ተጫራቶች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው።ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።

8. ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሽከርካሪዎች፣ በቁርጥራጭ መልከ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%) ፣ የተለያዩ የአገለገሉ ንብረቶች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲፒአ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።

9. የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ባዶ የቶነር ካርትሬጆችን በማሰባሰብ ፈጭተው መልሶ መጠቀም ለሚችሉ ሀገር በቀል የቶነር አምራች ፋብሪካዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በተመለከተ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም እንዲያሲይዙ።

10. የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል። ሆኖም የጨረታ መከፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።

11. ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም።

12. ተሽከርካሪዎች የነበረባቸው የቦሎ ዕዳ እና የስም ዝውውር ወጪ በአሸናፊ ተጫራቾች ይሸፈናል።

13. አንድ ተጫራች አንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ የመ/ቤት ንብረቶች በላይመግዛት ይችላል። ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪ፤ ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም።

14. ከመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።

15. የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሳይጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም።

16. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መከፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል፡፡

17. ንብረቱን በ10የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡

18. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም።

19. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

 

20. የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ባዶ የቶነር ካርትሬጆችን በማሰባሰብ ፈጭተው መልሶ መጠቀም (Recycle) ለማድረግ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሀገር በቀል የቶነር አምራች ፋብሪካዎች (ተጫራቾች) የቶነር ካርትሬጆችን ፈጭተው መልሶ መጠቀም (Recycle) የሚያስችል ፈቃድ፣ የአካባቢ ጥበቃ ይሁንታ ፈቃድና የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ነፃ ሰርተፊኬት፣ የኤሌከትሮኒከስ ቆሻሻ ማስወገድ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰርተፊኬትና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ያለው መሆን አለበት፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-81-22 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

Save Tender