የደ/ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለት/ክፍሎች እና ለስራ ሂደቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የደ/ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለት/ክፍሎች እና ለስራ ሂደቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ ሲሆን፡-
የጽህፈት መሳሪያ 7,000፣ አሌክትሪክ እቃዎች 12,000፣ ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች 12,000፣ ህንፃ መሳሪያ ፡-12,000፣ ጨርቃ ጨርቅ ፡4,000፣ የጽዳት እቃዎች 4,000፣ የመኪና እቃዎች እና ጎማ ፡ 10,000 በአቅርቦቱ መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች
- ተጫራቾች የዘመኑን ፍቃድ ያደሱ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተቱትን ፎርማቶች ሞልተው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በትክክል በመሙላት በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም ሙሉ ስም እና ፊርማ በማድረግ ኦርጅናል ኮፒ ተብሎ ለየብቻው ተፅፎበት በፖስታ በማሸግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በስራ ሰዓት በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን ሰነዱን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ይከፈታል። ሆኖም ግን ካላንደር በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በዚያው ሠዓት ታሽጎ ይከፈታል። በተጨማሪም በውስጥ ማስታወቂያ ጭምር ይገለፃል።
- አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- አሸናፊው ውል ገብቶ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅበታል።
- ግዥው ከ200,000/ከሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
- የግዥ መጠኑ 20,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ኮሌጁ የቫቱን ግማሽ ፐርሰንት ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑ ይታወቅ።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ማንኛውን ጥሬ እቃ ኮሌጁ መጋዘን ድረስ የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በውስጥ ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ከላይ በየሎቱ ፊት ለፊት በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጪ የሚቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋሉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የተዘጋጀውን ሰነድ እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ለኮሌጁ ገንዘብ ያዥ በመከፈል ጨረታው በጋዜጣ ከውጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 681 5616/ 011 681 2572/12
የደ/ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
