የቡታጅራ ውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በቡታጅራ አካባቢ ለውሃ ለአዲስ መስመር ጠያቂዎች አገልግሎት ላይ የሚውል የውሃ ቆጣሪ በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ አገልግሎት
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት ለውሃ መስመር ለአዲስ መስመር ጠያቂዎች አገልግሎት የሚውል
- የውሃ ቆጣሪዎች ፣
- የቧንቧና መገጣጠሚያ እቃዎች፣
የቡታጅራ ውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በቡታጅራ አካባቢ ለውሃ ለአዲስ መስመር ጠያቂዎች አገልግሎት ላይ የሚውል የውሃ ቆጣሪ በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ በፋይናንስ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃዎችን ከዋናው ጋር የተገናዘበ በፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
- የዕቃዎቹም የጨረታ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ቡታጅራ ከተማ ውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 10 በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመስስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የሚቻል ሲሆን አድራሻችንም ከቡታጅራ ንግድ ባንክ በስተጀርባ 20 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
- የሚጫረቱባቸው ዕቃዎች በመለየት በዓይነታቸው የሚሸጡባቸውን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚጫረቱባቸውን ዘርፍና የተጫራቹን ስም በግልፅ በመፃፍ የድርጅቱ ማህተም አርፎበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ሰነዱን በገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በእነዚሁ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከቀኑ 8፡00 በ16ኛው ቀን የጨረታው ሳጥኑ ታሽጐ ከቀኑ 8፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ ተጫራቾች/ ወኪሎቻቸው ባይኖሩም ጨረታው ከመክፈት አይታገድም፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠው ቼክ (C.P.O) ብቻ ከጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ አሸናፊው ድርጅት ውል እንደገባ ይመለስላቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን መስሪያ ቤቱ በወሰነለት ቀን ካላቀረበ ለጨረታ ማስመስከሪያ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- አሸናፊ ድርጅቶች ማሸነፋቸው እንደተገለፀላቸው ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን የግዢ ፈፃሚው አድራሻ ድረስ የሚያቀርብ መሆኑን እያሳወቅን መ/ቤቱ በወሰነለት ቀን ካላቀረበ ለጨረታ ማስመስከሪያ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስም፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ሊገኙ ባይችሉ መ/ቤቱ ጨረታውን ከፍቶ የሚያወዳድር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡-
Fax 251-461151792/ Mobile 0910966823
/0912475709 P.0.Box 16
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ አገልግሎት
