በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት በወናጎ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ ከተለያዩ ሴ/መ/ቤት በቀረበው ጥያቄ መሰረት በ2018 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ጨረታ ቁጥር 001/2018
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት በወናጎ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ ከተለያዩ ሴ/መ/ቤት በቀረበው ጥያቄ መሰረት በ2018 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መ/ቤቱ የሚገዛቸውን ዕቃዎች ዝርዝር የያዘ ሰነድ በሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ፤
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈለ /ከመንግሥት ዕዳ ነጻ የሆነ፤
- የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፤
- የ/VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው /TIN NO/፤
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤
- አሸናፊ ድርጅት መክፈል ያለበትን የሽያጭ ታክስ 3% ይከፍላል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ገንዘብ ልክ 10% ያስይዛል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን ከወናጎ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ በማይመለስ ብር 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ዋጋ አቅራቢ ተወዳዳሪዎች የዕቃ ዓይቱንና ደረጃውን በሰነዱ ዝርዝር በተቀመጠው ቅደም ተከተል ሞልተው አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ ቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ለብቻውን እንዲሁም ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኮፒ ለየብቻው በማድረግ ሁሉንም በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በባንክ በተረጋገጠ 20,000 ብር (ሃያ ሺህ ብር) ማስያዝ ያለበት ሲሆን፤ /CPO/ ለብቻው ታሽጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር መቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይተው በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት በመሰብሰብያ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0949159755/ 0932194807
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
