የጅማ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ኢንተርፕራይዝ በ2018 በጀት የውሃ ቱቦ እና ፊቲንግ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Jimma Town Water Supply and Sewerage Service Enterprise (የጅማ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ኢንተርፕራይዝ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጅማ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ኢንተርፕራይዝ በ2018 በጀት የውሃ ቱቦ እና ፊቲንግ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
-
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባችሁ በዘርፉ የተሰማሩ እና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት፤ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ በግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፍኬት: በአቅራቢነት የተመዘገቡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጅማ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ኢንተርፕራይዝ ዲፖ አካባቢ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ብቻ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣ እስከ 15ኛው የስራ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የውሃ ቱቦ እና ፊቲንግ እቃዎችን ብር 100,000 (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዛችሁ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣ በ15 ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጅማ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ እና ፋይናንስ ዳሬክተር ይከፈታል።
- ጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ተለይቶ ውል እስኪፈጽሙ እንደተያዘ ይቆያል።
- ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በድርጅቱ ስም የተዘጋጀውን በማስያዝ በአምስት ቀን ውስጥ ውል ተዋውሎ ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል። ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተውና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በገዙበት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን (VAT) ያካተተ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ለማስገባት በምትመጡበት ጊዜ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ 0913408503 ወይም 0911054052 ደውለው ይጠይቁ።
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ:- ተጫራቾች ሰነዱን ለመግዛት በምትመጡበት ጊዜ በመስኩ የተሰማራችሁበትን ንግድ ፍቃድ ኮፒ መያዝ እንዳትረሱ
የጅማ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ኢንተርፕራይዝ
