በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ ለቢሮ አገልግሎት የሚሆን ሎት 1 የህንፃ ግንባታና ጥገና፣ ሎት 2 የመድሀኒትና የላብራቶሪ ሪጄንቶችን መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ ለቢሮ አገልግሎት የሚሆን ሎት 1 የህንፃ ግንባታና ጥገና፣ ሎት 2 የመድሀኒትና የላብራቶሪ ሪጄንቶችን መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያለው/ላት ፡፡
- በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ ፡፡
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን አይነት የማይመለስ ብር በየሎቱ / ለአንድ ሎት /200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ።
- ከካሽ ሪጅስተር ውጭ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ብቻ የምትጠቀሙ ተጫራቾች ከገቢዎች እንደትጠቀሙ የተፈቀደበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ማቅረብ የማትችሉ ተጫራቾች ተወዳድረው ቢያሸንፉ ክፍያ የማይፈፀም መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከበሪያ ለሚጫረቱበት አይነት ለእያንዳዱ በሎት ቢድ ቦንድ / በሲፒኦ /CPO/ 1000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በየአንዳዱ ሎት ኦርጅናል እና ኮፒ ለየ ብቻ ታሽጎ ዘወትር በስራ ሰዓት እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል ፡፡
- ተጫራቾች በምትጫረቱባቸው እቃዎች ላይ ሳምፕል (ናሙና) ዲዛይን የሚቀርብባቸው ዕቃዎች በተቋሙ ማግኘት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን 10 % የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባችዋል።
- የጨረታው ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከዋለ በኋላ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን በአላትና የእረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በሚቀጥሉት የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ በግልፅ ይከፈታል ፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስክ ቁጥር፡- 01-18-93-20-89
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ
