Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት በኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር በ2018 በጀት አመት በተያዘው ለመምሪያው አገልግሎት የሚውል የቋሚ ዕቃ ማለትም LED PROJCTOR በግልጽ ጨረታ በማውጣት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት በኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር በ2018 በጀት አመት በተያዘው ለመምሪያው አገልግሎት የሚውል የቋሚ ዕቃ ማለትም LED PROJCTOR በግልጽ ጨረታ በማውጣት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ይችላሉ ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው
  3. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን እስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በመሄድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ 11/30 ድረስ ከ5/03/2018 እስከ) 19/03/2018 ዓ/ም ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በcpo /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 12,000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን cpo /ሲ.ፒ.ኦ/ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. የቋሚ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይቻላል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት 22/03/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቾች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ጊዜ የበዓል ቀን ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ውጪ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
  11. በጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባችኋል።
  12. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲገጥማችሁ አሰሪው መ/ቤት ጨረታ ካወጣው አካል ከጨረታው መክፈቻ እለት በፊት በስልክ ቁጥር 0333511042 / 0987023998 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. ጨረታው ለ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  14. የጨረታው ውድድር በጠቅላላ ዋጋ ሎት ድምር ነው፡፡
  15. መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

 

Save Tender