በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ ሎት 1፡- ኤሌክትሮኒክስ (ላፕቶፕና ሞባይል ቀፎ) እና ሎት 2፡- ሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት/ተጫራች መግዛት ይፈልጋል።
መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ ሎት 1፡- ኤሌክትሮኒክስ (ላፕቶፕና ሞባይል ቀፎ) እና ሎት 2፡- ሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት/ተጫራች መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin No/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንት ዋስትና/ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው።
- በጋዜጣው የወጣው ግልጽ ጨረታ በብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀርበግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት። እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (CPO) ቫትን ጨምሮ ማስያዝ አለበት። ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ።
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረገ እና ለጨረታ የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መገዛት ይቻላል።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል።
- ቅዳሜ የዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው ተወዳዳሪዎች ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆንተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያገደውም።
- የጨረታ አሸናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10%/አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት።
- ከአንድ ሎት ውስጥ ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፤ አሸናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል። አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል/ይሸፍናል።
- የሚገዛን ንብረት (እቃ) ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም የወዛደር ማሳጫኛ እና የትራንስፖርት ውጪ በአሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል። የሚገዛ እቃ ብዛት እና የጥራት መጠን ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል።
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሃሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ኅ/ስ/ማኅበር የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር፡- 09 11 59 05 34 /09 10 63 46 46 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ
