በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች ስራ አገልግሎት የሚሆን በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገነቡ የውሃ ቦኖ /ማደያ፣ የውሃ ቦኖና መስመር ዝርጋታ፣ ምንጭ በመስመርና ምነጭ በቦታ ማጎልበት ግንባታዎች፣ የተማሪዎች መማሪያ ክፍል ግንባታ፣ የመንገድ ዲዛይን ስራ፣ ለመንገድ ጠረጋ ስራ አገልግሎት የሚሆን ማሽነሪ ኪራይና የውሃ መስመር መገጣጠሚያና ግንባታ ዕቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች ስራ አገልግሎት የሚሆን በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገነቡ የውሃ ቦኖ /ማደያ፣ የውሃ ቦኖና መስመር ዝርጋታ፣ ምንጭ በመስመርና ምነጭ በቦታ ማጎልበት ግንባታዎች፣ የተማሪዎች መማሪያ ክፍል ግንባታ፣ የመንገድ ዲዛይን ስራ፣ ለመንገድ ጠረጋ ስራ አገልግሎት የሚሆን ማሽነሪ ኪራይና የውሃ መስመር መገጣጠሚያና ግንባታ ዕቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋነት /VAT/ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በግንባታ ዘርፍ በBC፣ GC እና በውሃና ውሃነክ ስራዎች በጨረታ መመሪያው ላይ በተገለጸው ደረጃና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ግንባታ፣ አቅርቦትና ኪራይ ዓይነት፣ ስራ ዝርዝር፣ ቦታ፣ ፕላን፣ ዝርዝር መግለጫና መመሪያ የያዘ የጨረታ ሰነድ ከመ/ቤታችን ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግንባታ በጨረታ መመሪያው የተገለጸውን የገንዘብ መጠን በባንክ የተረጋገጠ ትእዛዝ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ/መሂ1 ኮፒ ተቆርጦ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዢ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምር ለግንባታና ዲዛይን ስራ አገልግሎት እስከ 22ኛው ቀን ለማሽን ኪራይና የውሃ መስመር ዕቃዎች እስከ 16ኛው ቀን 4:00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግንባታዎችና ዲዛይን ለተከታታይ 21 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን በመ/ቤታችን ግዢ ቢሮ ቁጥር 3 4፡00 ሰዓት እና ለማሽነሪ ኪራይና ለውሃ መስመር እቃዎች አቅርቦት ለተከተታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በመ/ቤታችን ግዢ ቢሮ ቁጥር 3 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። ሆኖም ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን። ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት፣ በስልክ ቁጥር 011-11-90-270/280 +251997041395 በመደወል ወይም በTelegram channel @t.me/Ensarowereda ወይም gmail አካውንት ensaroweredafinanceoffice@gmail.com መላክ ይችላሉ።
የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዢና ንብረት አስተዳደር ቡድን (ለሚ)
