የህዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በሮድ-ፈንድ በጀት ጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ስራ ከሎት 001/2018 እስከ ሎት 007/2018 ድረስ ያሉት 7 ሎቶችን 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ልማት መምሪያ
የህዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በሮድ-ፈንድ በጀት ጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ስራ ከሎት 001/2018 እስከ ሎት 007/2018 ድረስ ያሉት 7 ሎቶችን 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት በዘርፉ ከተደራጁ ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራና አሰሪ ሰራተኛ መምሪያ አደራጅተው የላካቸው ማህበራት መወዳደር ይችላሉ፡፡
በገጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ስራ ዘርፍ ተደራጅቶ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት ፤
1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
2. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፤
3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
4. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ፡፡
6. የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት በፋይ ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
9. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል ከ5% (ከአምስት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
10. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከ አሥራ አምስት ፐርሰንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
11. ለጨረታ ያስገበ-ት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች (ከ20%-30%) ከሃያ እስከ ሰላሳ ፐርሠንት በታች መውረድ የለበትም፡፡
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
