Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-11-25 00:00:00
  • Categories Vehicle Spare Parts

የሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት የመኪና ዕቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04/2018

የሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት የመኪና ዕቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መሰረት ጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

1.ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና Tin No ቁጥር ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡

2.የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3.ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ነው፡፡

4.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ይታሸግና ወዲያውኑ በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

5.15%/ VAT ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡

6.ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ለይተው በሁለት ፖስታ በማድረግ በሴም ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የመወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ አንቀፅና ሁኔታ ላይየተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም አሸናፈው ድርጅት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላሳዩ ግዥዎች ላወጣው ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

8.የቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳቦች በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፀንቶ የሚቆዩ ማስተካከያ የማይደረግ መሆናቸውን እናረጋግጣለን፡፡

9. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ሽያጭ 2% ብር ከባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለበት፡፡

10. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ/ብር ብቻ) በመክፈል ከኤጀንሲው ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይቻላል፡፡

11.ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ከዚህ የመወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ ጋር የተያያዘ የቀረበ ተጨማሪ ሰነድ የተጫራቾችን ፊርማና ማህተም ይፈልጋል፡፡ ጨረታ ሰነድ ላይ ያሉ ሁኔታዎች ከሁሉም በላይ በመወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ የቀረቡትን ሌሎች ተጨማሪ ማረጋገጫዎች ፈርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው መወዳደሪያ ሃሳብ ይሰረዛል፡፡

አድራሻ፤

በኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጎን

ሀዋሳ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0916020865/0949105209/0916516908

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ

Save Tender