በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በሕጋዊ ኤጀንሲ የጥበቃ ሠራተኛን በተለያየ የውሃ ጉድጓድ ጣቢያ በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።
በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በሕጋዊ ኤጀንሲ የጥበቃ ሠራተኛን በተለያየ የውሃ ጉድጓድ ጣቢያ በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያማሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፤
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ
3. ኤጀንሲው ከላይ የተጠቀሱትን የሚገልፅ ማስረጃዎች ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤
4. ኤጀንሲው የጨረታው ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ይህ ማሰታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት/15/ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል 9 ቁጥር ገቢዎች ዳይሬክቶሬት ሰነድ መውሰድ ይችላሉ
5. ኤጀንሲው የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር(ሰነድ) እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ /በፖስታ/ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት(15) ተከተታይ የስራ ቀናት እና በስራ ሰዓት በሸገር ከተማ የመጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ ባዘጋጀነዉ የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፤
6. ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት በሸገር ከተማ የመጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ ይከፈታል ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
7. ኤጀንሲው ለጨረታ ማስከበሪያ 1% ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ ወይም C.P.O ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት
8. የስራው አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
9. ዊዝ ሆልድ ታከስ ለመቁረጥ ፈቃደኛ የሆነ
10. የጨረታ ሣጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0113 381383/0942708556
በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
