በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግድ ወረዳ እንስሳት ሀብት ጽ/ቤት በአልማ በጀት የማህበረሰብ አቀር መድሃኒት ቤት አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግድ ወረዳ እንስሳት ሀብት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የእንስሳት ህክምና ቁሳቁስ ግዥ በተዘዋዋሪ በጀት የእንስሳት መድሃኒት ግዥ በወግዲ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ስር ወግዲ ቁጥር 1 ት/ቤት በመደበኛ በጀት የቅድመ አንደኛ /አፀደ ህፃናት/ መማሪያ ክፍል አጠቃላይ ወጭ ችሎ ማስገንባት እና የወግዲ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በአልማ በጀት የማህበረሰብ አቀር መድሃኒት ቤት አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤታችን ይጋበዛል። በዚህም መሰረት ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የዘመኑ የታደሰና ህጋዊ ፈቃድ ያለውና የንግድ ስራ ዘርፉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ነምበር ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የግዡ መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ ላይ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው የንግድ ስራ ፍቃድ ኮድ መሰረት ንግድ ፈቃዳቸውን ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን ድረስ ብር 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ መጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመድሃኒት እና ለመድሃኒት ቁሳቁስ ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እና ለግንባታ ደግሞ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በመግዛት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጂናል ፖስታ እና ኮፒ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚያው በ22ኛው ቀን ጨረታው 4:00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን ይከፍታል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸላቸው ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት በወግድ ወረዳ እንስሳት ሀብት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የእንስሳት ህክምና ቁሳቁስ ግዥ 2,000 ብር /ሁለት ሺህ ብር/, በተዘዋዋሪ በጀት የእንስሳት መድሃኒት ግዥ ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ ለአፀደ ህፃናት የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ዋጋ 10 ፐርሰንት እና ለማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት ቤት ግንባታ ደግሞ የሞሉትን ዋጋ 1.0 ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ነጠላ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይገባዋል ካለው ደግሞ ከጨረታ ውጭ ውድቅ ይደረጋል።
- ውድድሩ በጥቅል ድምር (ሎት) መሆኑን እንድያውቁትና የሁሉንም አቃዎች ዋጋ መሙላት የሚጠበቅብዎት መሆኑን አይዘንጉ።
- ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ፀንቶ የመቆያ ጊዜ 30 ቀን መሆኑ ይታወቅ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
