Tender Detail

Tender Details


የደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለውሃ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በየሎቱ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

የደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት


የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለውሃ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በየሎቱ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የብረት ቧንቧ፣ የብረትና የፕላስቲክ ቧንቧ መገጣጠሚያዎች በተናጠል ግዥ፣

ሎት 2 የጽሕፈት መሣሪያዎች በተናጠል ግዥ፣

ሎት 3 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ በተናጠል ግዥ

ሎት 4. የተዘጋጁ የደንብ ልብስ አልባሳት በተናጠል ግዥ፣

ሎት 5 የጽዳት ዕቃዎች በተናጠል ግዥ፣

ሎች 6 ኤሌትሪካል ዕቃዎች በተናጠል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት፡- መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሠዳደርየምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤

2 የሚሞላው የዕቃ ዋጋ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው፣

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከሎት፡ እስከ ሎት 6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው::

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. የጨረታ ሰነዱ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በደብረሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ 5 መግዛት ይችላሉ፣

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 19% በጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ባንከ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ CPO ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::

8. ተጫራቹ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ያሉትን ሰነዶች በየአንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፣ ስም፣ ፊርማ እና አድራሻ ስልክ ቁጥር በማስፈር ኦርጅናል የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ አሸገው የጨረታ ሳጥኑ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ በደብረሲና ከተማ አስተዳደርውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በግ/ፍ/ን/አስተዳር ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ በቀጣይ የሚከፈት ይሆናል፡፡

 

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰዕረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጽ/ቤታችን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0116800478) 0920856115/በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

11. ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ሳንፕሎቹን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል::

ተጫራቹ በውድድ የማይሳተፍ መሆኑን ጽ/ቤቱ ያሳውቃል ::

12. ለዋና መስመር፣ ለአነስተኛ እና ለመካከለኛ የውሃ ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል የብረት ቧንቧ፣ የብረት እና የፐላስቲክ ቧንቧ መገጣጠሚያዎች ፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የተዘጋጁ የደንብ ልብስ አልባሳት፣ የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ኤሌክትሪካል ዕቃዎች /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

13 ለበለጠ ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ በማንበብ መረዳት ይቻላል::

በአብክመ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የደ/ሲና ከተማ አስተዳደር

መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት

Save Tender