Tender Detail

Tender Details

  • Company East African Lion Brands Manufacturing S.C. (ኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግስ አ.ማ)
  • Address ቢሾፍቱ ወረዳ ዲባዩ ቀበሌ ደካ ቦራ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0926260203
  • Websitehttps://eastafricanlionbrandsmanufacturing.com/
  • Deadline20 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋውን ሁለት ፐርሰንት (2%)
  • opening date2025-11-20 00:00:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products

ኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግስ አ.ማ በመጋዘን ውስጥ ተከማችተው የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ልዩ ልዩ ማሸጊያ ካርቶኖች እና ፕላስቲክ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

East African Lion Brands Manufacturing S.C. (ኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግስ አ.ማ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግስ አ.ማ በመጋዘን ውስጥ ተከማችተው የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ልዩ ልዩ ማሸጊያ ካርቶኖች እና ፕላስቲክ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የእቃ አይነቶች ዝርዝር

መለኪያ

ብዛት

1

የተለያዩ ማሸጊያ ካርቶኖች

በኪሎ

40,000.00

2

የተለያዩ አይነት የፕላስቲክ እቃዎች

በኪሎ

7,000.00

3

የሳኒታዘር ማሸጊያ ጃር ከነ ክዳኑ 50cc

በፍሬ

648,912.00

4

የሳኒታዘር ማሽጊያ ጃር ከነ ክዳኑ 100cc

በፍሬ

1,368,735.00

5

የሳኒታዘር ማሸጊያ ጃር ከነ ክዳነ- 500cc

በፍሬ

199,973.00

 

ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያ የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት ፐርሰንት (2%) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የአካዉንት ስም ኢስት አፍሪካ ላየን ብራንድስ አ.ማ (East Africa Lion Brands Manufacturing SC) ገቢ አድርገዉ ማቅረብ አለባቸዉ። የጨረታ ማስከበርያዉ ላሸናፊዉ ከሚገዛዉ እቃ ላይ ታሳቢ ሲደረግለት ለተሸናፊዉ ወድያዉ ይመለስለታል። ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፍቃድና የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን ሰርተፍኬት) ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ድርጅቱ ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በ500 (አምስት መቶ) ብር በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል። በተራ ቁጥር አንድና ሁለት ያሉት እቃዎች የድርጅቱን ብራንድ የያዙ ስለሆነ ተጫራቾች ፈጭተዉ የሚጠቀሙ ወይም ካርቶን የማምረት ፍቃድ ያላችዉ እና ፕላስቲክ የማምረት ፍቃድ ያላቸዉ መሆን ይጠበቅባችዋል ይህንን የሚገልፅ ፍቃድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ በተጨማሪም የእቃዎቹን ብራንድ ስም ላለመጠቀም የሽያጭ ዉል ላይ ግዴታ ይገባል። የጨረታ ሳጥኑ ሀሙስ ህዳር 11 2018 ዓም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 9:15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢስት አፍሪካ ላየን ብራንድስ ማኒፋክቸሪንግ አክሲዮን ማህበር መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በግልፅ ይከፈታል እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታውን በሚከፍትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ቢሾፍቱ ወረዳ ዲባዩ ቀበሌ ደካ ቦራ (ለበለጠ መረጃ በስቁ 0926260203/0962810807 መደወል ይችላሉ)

ድርጅቱ

 

Save Tender