Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር
  • Address በካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0476680500
  • Website
  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price800.00
  • Bid Security200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ /ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ህንፃ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል።

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2018

 

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ /ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ህንፃ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. የVAT ተመዝጋቢ፣ TIN ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በመ/መ/ቤት አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ደረጃ 5 BC/GC እና ከዚያ በላይ የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችልና የስራ ፍቃዱ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስተር እና በክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ህጋዊ ማረጋገጫ የተሰጠው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምችል ሆኖ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 800 /ስምንት መቶ ብር/ እየከፈለ ከሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ላይ ዘወትር በሥራ ሠዓት የድርጅታቸውን ዶክመንት ኮፒ ይዘው በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ኦርጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል ከሁለት ሁለት ኮፒዎች ጋር ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደ ፋይ/ቢ/ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  3. እያንዳንዱ ተጫራቾች መወዳደር የምችሉት ከስራ ፍቃዳቸው ውጭ መወዳደር እና የሌላውን ተወዳዳሪ ተንተርሶ ዋጋ መመላት አይቻልም-
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ቢ/ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው። ጨረታ በ31ኛ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል በዕለቱ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን (CPO) ለተሸናፊው ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ማሸነፉ ከተግለጸበት ቀን አንስቶ እስከ 7ኛው ቀን ድረስ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  7. የጨረታው መዝግያና መክፈቻ የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

 

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0476680500/0917950945 በመደወል መረዳት ይችላል።

 

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር

 

Save Tender