የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የቢሮ ጥገና፣ የመኪና ማቆሚያ፣ የአጥር ሥራ፣ እና የካፍቴሪያ ግንባታ ስራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የቢሮ ጥገና፣ የመኪና ማቆሚያ፣ የአጥር ሥራ፣ እና የካፍቴሪያ ግንባታ ስራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2017 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮንስትራከሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ፡፡
- በሲዳማ ክልል ውስጥ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ስራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፣
- በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተው ያላስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
- የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው! ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (BANK GAURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ፋይናንስ ክፍል በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
- የጨረታው ሰንድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድረሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም።
- አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀስው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ
ሀዋሳ ከተማ
