ድርጅታችን የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት በ2018 በጀት አመት የተለያዩ የደንብ ልብስ ጨርቆችና የተለያዩ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Ethiopian Tourist Trading Enterprise (የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት)
የተለያዩ የደንብ ልብስ ጨርቆችና የተስያዩ አልባሳት ግዥ
ጨረታ ቁጥር 001/2018
ድርጅታችን የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት በ2018 በጀት አመት የተለያዩ የደንብ ልብስ ጨርቆችና የተለያዩ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደርየምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ የገብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት የገብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት በጨረታ ተካፋይ ለመሆን መቻላቸውን የሚገልፅ ከሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤና በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባስስልጣን አቅራቢዎች ድረ-ገፅ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ 50,000.00 /ሃምሳ ሽህ ብር/ በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
3. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00-6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30-11፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ሁስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በድርጅቱ ግዥ ንብረት አስተዳደርና ቴክኒክ ዳይሬክቶሬት ቢሮ 2ኛ ፎቅ እስከ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን አስከ 4:00 ሰዓት በመከተት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ ከአክሱም ሆቶል ጀርባ ፍቅሬ ኩንስፓኛ ፊት ለፊት
በስልክ ቁጥር 0914 341342 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት
