በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብረካ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል መጠኑ 82,000 (ሰማንያ ሁለት ሺህ) ቶን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ ጨረታ ቁጥር
ሙሲፋ/03/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብረካ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል መጠኑ 82,000 (ሰማንያ ሁለት ሺህ) ቶን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፉድርጅቶች በዘርፉ የተሰማሩ አምራችወይምአቅራቢመሆናቸውን የሚገልፅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸው አምራች ከሆናችሁ ከከልል መንግስታት የተሰጠ የማዕድን ማምረት ስራ ፍቃድ ሰርተፊኬት አቅራቢ ከሆኑ የአቅራቢነት ፍቃድ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የተጨማሪ እሴት ታከስ እና የታክስ ከፋይተመዝጋቢ የሆኑ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ የድንጋይ ከሰል ምርመራ ውጤት እና ይዞታ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ፣(አስገዳጅ መስፈርት ሲሆኑ አሟልቶ ያላቀረበ ከጨረታው ይሰረዛል ) ስለዚህ የተመቀሱትን ማስረጃዎች፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስና የታክስ ከፋይ ምዝገባ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመልስ ብር 575.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህነፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር ) በኬሚካል እንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብረካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም በባንከ በተረጋገጠ ቼከ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴከኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው በዕለቱ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል :: ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር 0114420216
ኢክስ 0114420688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር
ሲሚንቶ ፋብሪካ
