የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት የተዘጋጁ ልዩ ልዩ የፋይናንስ አፈጻጸም መመሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በማዕቀፍ ስምምነት ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 02/2018
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት የተዘጋጁ ልዩ ልዩ የፋይናንስ አፈጻጸም መመሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በማዕቀፍ ስምምነት ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ፤
- በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌይብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት 90 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ለጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የንግድ ፍቃዳቸውን ኮፒውን በማቅረብ ከክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ/ንብ/ አስ/ዳይሬከቶሬት ሥራ ከፍል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ 3፡45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 11ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ከላይ በተባለው ሰዓት 3፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፈው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ 05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የህትመት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
