በደቡብ ምዕራብ ኢት/ህ/ክ/መንግስት በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መጸዳጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
በደቡብ ምዕራብ ኢት/ህ/ክ/መንግስት ዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢት/ህ/ክ/መንግስት በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በኮ-ዋሽ ፕሮግራም
1ኛ በአሠሊ ትም/ት ቤት፡- የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ የመምህራን መጸዳጃ ቤት፣ የወንድ ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት፣ የሴቶች መጸዳጃ ቤት 2ኛ-ደሺ ትምህርት ቤት፡- የመምህራን መጸዳጃ ቤት፣ የወንድ ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት፣ የሴቶች መጸዳጃ ቤት፣ 3ኛ-ማይላ ትም/ት ቤት፡- የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ 4ኛ-ኦቻ ጤና ኬላ፡ መጸዳጃ ቤት፣ 5ኛ-ሴሪ ደንጋ ትም/ት ቤት መጸዳጃ ቤት፣ 6ኛ ወንባ ቀበሌ ጤና ኬላ፡ መጸዳጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል። በዚህ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውንም በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው ተጫራች ማሟላት ያለባቸው፤
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ሥራ ፍቃድ ያለው/ያላት
- በዘርፉ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
- የዘመኑን ግብር የከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ቫት /ተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ የሆኑ
- መልካም ሥራ አፈጻጸም ያለው/ያላት
- ደረጃ 4፤ 5፤ 6፤ 7፣ 8 እና 9
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በእያንዳንዱ ጨረታ 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር በጥሬ/ cpo ብቻ በ1ኛው ኮፒ ጨምሮ ተጫራች የጨረታ አርጅናልና 2 ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በእናት ፖስታ ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም የጨረታ ሰነድ በኛ ኮፒ ውስጥ ማቅረብ አለበት ከዚህ ውጪ ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- ተጫራች በሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ስም፣ ማህተም መኖር አለበት።
- መ/ቤቱ በበጀት በጊዜ ለመጠቀም ከ2-3 ጨረታ በላይ እንዳያልፍ ሊከለከል ይችላል።
- ከዚህ በፊት ተወዳድሮ አልፎ በጊዜ ጨርሶ ያለስረከበ ተጫራች/ኮንትራክተር መ/ቤቱ ከውድድሩ ውጪ ሊያደርግ ይችላል።
- በሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራች ባቀረቡት ማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የዋጋ ለውጥ/ ማስተካከያ ማድረግ ወይም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- የጨረታ ሥራን ሆን ብሎ ከጨረታ ማሸጊያ ጊዜ እስከ ጨረታ ማጠናቀቂያ ድረስ መረበሽ ጨረታ ውጪ ያደርጋል።
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት 16ኛ ቀን 1ኛ የተጠቀሱ ጨረታዎች፡ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ 4፡00 ታሽጎ 4፡20 ይከፈታል፤ የመምህራን መጸዳጃ ቤት 4፡30 ታሽጎ 4፡45 ይከፈታል። የወንድ ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት ታሽጎ 5፡20 ይከፈታል። የሴቶች መጸዳጃ ቤት 5፡30 ታሽጎ 5፡45 ይከፈታል።
- 2ኛ-ደሺ ትምህርት ቤት -የመምህራን መጸዳጃ ቤት 7፡30 ታሽጎ 7፡45 ይከፈታል፤ የወንድ ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት 8፡10 ታሽጎ 8፡25 ይከፈታል። የሴቶች መጸዳጃ ቤት 8፡40 ታሽጎ 8፡50 ይከፈታል። 3ኛ-ማይላ ትም/ት ቤት፡- የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ 9፡10 ታሽጎ 9፡20 ይከፈታል። 4ኛ-ኦቻ ጤና ኬላ፡ መጸዳጃ ቤት 9፡30 ታሽጎ 9፡40 ይከፈታል። 5ኛ ሴሪ ደንጋ ትም/ት ቤት መጸዳጃ ቤት 9፡50 ታሽጎ 10፡00 ይከፈታል። 6ኛ-ወንባ ቀበሌ ጤና ኬላ፡ መጸዳጃ ቤት 10፡10 ታሽጎ 10፡20 ይከፈታል። በዚህ ሰዓት ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢት/ህ/ክ/መንግስት ዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በመጀመሪያው ሥራ ቀን ይፈታል።
- በዕለቱ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም።
- ተጨማሪ ማረጃ ቢያሥፈልግ የስልክ ቁጥር በ 09 13 31 24 99/ 09 77 91 91 61/ 09 35 12 65 76 ይደውሉ።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆኑ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በዳውሮ ዞን የማሪ ማንሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
