ኮበል ኢንዱስትሪ አ/ማ በ2018 በጀት ዓመት ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ጉድጓጓድ ቁፋሮ (አንድ ከዋናው ግቢ እና አንድ ከእንስሳት ማድለቢያው) በዘርፉ ፍቃድ ካለው ድርጅት መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
Kobel Industry S.C (ኮበል ኢንዱስትሪ አ.ማ)
የድጋሚ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥርግአጠ-1/2018
ኮበል ኢንዱስትሪ አ/ማ በ2018 በጀት ዓመት ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ጉድጓጓድ ቁፋሮ (አንድ ከዋናው ግቢ እና አንድ ከእንስሳት ማድለቢያው) በዘርፉ ፍቃድ ካለው ድርጅት መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሕጋዊ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል፡፡
- የውሃ መቆፈር ፍቃድ ያለው
- በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን የፋናንሻል እና የቴክኒካል የዶክመንት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- አጠቃላይ ስለ ከርሰ ምድር ውሃ ጉድጓጓድ ቁፋሮዎቹ ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) በመክፈል ኮበል ኮርፖሬት የግዥ አቅርቦት እና ጠቅ/አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በመውሰድ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ተእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በቼክ ማስያዝ አለባቸው።
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በግዥ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኮርፖሬት የግዥ አቅርቦት እና ጠቅ/አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 (ሃያ አንደኛው) ተከታታይ ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አጠቃላይ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከመጫረቻ ሰነዱ ያገኙታል። ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ኮርፖሬት የግዥ አቅርቦት እና ጠቅ/አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0970244289/0918641242 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ኮበል ኢንዱስትሪ አ/ማ ባህርዳር ዓባይ ማዶ ቀበሌ 11 ትራፊክ መብራቱ ጎን ዋና መስመር ላይ
ኮበል ኢንዱስትሪ አ/ማ
