በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የአፈር ማከሚያ የግብርና ኖራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም ይፈልጋል
አገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም (RLLP 11) በአለም ባንከ የበጀት ድጋፍ በግዥ መለያ ቁጥር ET-AMHARA BOA‐502734_GO_RFB በፕሮጀክቱ ለታቀፉ ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል የአፈር ማከሚያ የግብርና ኖራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፤
- በማእድን ቢሮ/ሚኒስተር የግብርና ኖራ እንዲያመርቱ የተሰጣቸውን የታደሰ የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና ምንጩ፡ የኖራ ድንጋይ የሆነ እንዲሁም በ2018 ዓም የተሰራ የአፈር ማከሚያ ኖራ የላብራቶሪ ውጤት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር 200.000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ. ቁ 1_3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዛው የአፈር ማከሚያ የግብርና ኖራ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዕቃ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንታቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው የሚከተለው የአንድ ፖስታ ስርአት በመሆኑ ማንኛውም ተጫራች የቴክኒካል ፡ የፋይናንሻል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪ ያውን በአንድ ላይ በማድረግ በሁለት ፖስታውች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንታቱ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 (ሰላሳ) ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቀው ኖራ ማቅረቢያ የሚጠቀሙበትን መቋጠሪያ ላምኔትድ የሆነ ቀረጢት አንድ ናሙና ለብቻው በአንድ ፖስታ አሽገው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 31ኛ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ በግልጽ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዘወትር በስራ ሰአት ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 5849 / 058 320 8095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው እና በጨረታ ሰነዱ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
