በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ሳር ቤት በሚገኘው ቢሮ መግቢያ ላይ የድርጅቱን ሥም የሚጠቅስ ዲጂታል ማስታወቂያ በሚቀርብለት እስፔክ መሠረት በጋዜጣ በማውጣት አጫርቶ ማሰራት ይፈልጋል።
Oromia Investment and Industry Bureau (የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ሳር ቤት በሚገኘው ቢሮ መግቢያ ላይ የድርጅቱን ሥም የሚጠቅስ ዲጂታል ማስታወቂያ በሚቀርብለት እስፔክ መሠረት በጋዜጣ በማውጣት አጫርቶ ማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT / ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘው የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ሣር ቤት የሚገኘው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ 1ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሁለት የተለያዩ ፓስታ በማሸግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዛጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 21ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ 5:00 ሰዓት ይከፈታል በዕለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- የሚያሰራውን ሥራ 20% የጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ተጫራቾች ሥራውን በተባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አድራሻ :- በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሣር ቤት በሚገኘው ህንፃ 1ኛ ፎቅ
ለተጨማሪ ማብሪሪያ
በስልክ ቁጥር 0111-385-24-82/0913152039/0917805333 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ
