በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ከ/ከተማ የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ የተለያዩ የጥገና ስራዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ/ክ/ከተማ የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ከ/ከተማ የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ የተለያዩ የጥገና ስራዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቶች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. ንግድ ፈቃድ ያደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
3. ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢና አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተጫራቶች የምስከር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው::
4. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 4ተኛ ፎቅ ቢቁ 408 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሂሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው፡፡
6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል ኦሪጅናል፣ ፋይናንሻል ኮፒ፣ ቴክኒካል ኦሪጅናል ማለትም ኮፒ የሆኑ ህጋዊ ሰነዶች ላይ ማህተም የተመታ፣ ቴከኒካል ኮፒ እና የሚወዳደሩበትን አይነት በ4 ፖስታ ፋይናንሻል ኦሪጅናል፣ ፋይናንሻል ኮፒ፣ ቴከኒካል ኦሪጅናል፣ ቴክኒካል ኮፒ በፖስታው ላይ በመለየት ማህተም በመምታት እና በመፈረም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 408 በመገኘት ለዚህ የተዘጋጀው የተጫራቾች ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 408 በኮሚቴዎች ይከፈታል፡፡
8. እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት እና ሙሉ ሰነዱን ሳይገነጠል መመለስ አለበት፤ ይህን ያልተገበረ ተጫራች ውድቅ ይደረጋል፡፡
9. መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ተጫራቶች በጨረታ ለመካፈል ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ በመስሪያ ቤቱ ስም ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ከዚህ ውጪ የሚመጡ የጨረታ ማስከበሪያ አንቀበልም፡፡
11. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተካተተውን መረጃ በሙሉ ሞልተው መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
12. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉትን ስራ 10% ለአሸነፉት ስራ የውል ማስከበሪያ የሚያስይዙ መሆኑን ማወቅ አላበቸው፡፡
13. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟላ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከርና ጨረታውን ለማሳሳትና ለማጭበርበር የሚሞከር ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል፡፡
14. ተጫራቾች ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሳምፐል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
15. ማንኛውም ተጫራች CPO ቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ላይ አብሮ ማስገባት አለበት፡፡
አድራሻ፡- በአዲሱ የካራ መንገድ ከአቅም ግንባታ ጀርባ እና ወሰን ግሮሰሪ 200 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር:- 011-8-93-25-88/011-8-93-22-55/011-8-93-29-88
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ
