አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የግንባታና ተያያዥ ስራዎች የማማከር አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ መወዳዳሪያ ሀሳብ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል፡፡
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
የሀገር ውስጥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር፡- 001/2018 ሎት 01
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የግንባታና ተያያዥ ስራዎች የማማከር አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ መወዳዳሪያ ሀሳብ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል፡፡
በዚሁ መሰረት-
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በe-GP በድረ-ገጽ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ከግብር ነፃ ስለመሆናቸው ከሊራንስና ሌሎች አስፈላጊ ዶከሜንቶችን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ፍላጎታቸውን ሊያቀርቡ የሚያስችላቸውን መረጃ እንዲያገኙ የምከር አገልግሎት ስራውን ዳራ፣ ዓላማ፣ ግብ እና የማማከር አገልግሎቱ ወሰን እና ሌሎች ለአገልግሎቱ አስፈላጊ የሆኑትን መግለጫዎች የሚዘረዝር ቢጋር/ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 5 የስራ ቀናት ድረስ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የግዥ ስራ አስፈጻሚ በዩኒቨርሲቲው ቢሮ በአካል ቀርበው ለማማከር አገልግሎት የተዘጋጀውን የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ መወዳዳሪያ ሀሳብ/በጋር/TOR/በነፃ ወስደው ፍላጎታቸውን ሞልተው መመለስ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሚሞሉትን የተዘጋጀውን የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል ህጋዊነትና ቴከኒካል ሰነድ የያዘ እና አንድ ህጋዊነትና ቴከኒካል ኮፒ በተለያየ የታሸገ ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር122 ግዥ ስራ አስፈጻሚ በአካል በማቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ተከታታይ ቀን ተቆጥሮ በ6ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 122 ግዥ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ላይ ይከፈታል፡፡ 6ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡
5. የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ መወዳደሪያ ሀሳብ ጨረታ ላይ የሚሳተፉት ተጫራቾች በዚህ ዙርየጨረታ ዋስትና እና ዋጋ እንዲያቀርቡ አይጠየቁም፤ ፍላጎታቸውን ያሳወቁ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት መረጃ ተገምግሞ የተፈለገው የምከር አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ይደረጋል፡፡
6.ተጫራቾች በጨረታው መከፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባይገኙ የጨረታውን መከፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
7. ዩኒቨርስቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልከ ቁጥር፡ 251578875050/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
