የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የስቱዲዮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የስቱዲዮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ፍላጎትና አቅም ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች ህጋዊና የታደስ ወይም አዲስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውንና የታከስ ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና የተመዘገቡ መሆኑን እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የጨረታው ሰነድ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 -11:00 ሰዓት አዲስ አበባ ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የጽ/ቤቱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብቻ/ በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
3. የጨረታው ሰነድ አንድ ሎት ያለው ሲሆን፣ ተወዳዳሪዎች በሁለት የተለያዩ ኤንቨሎፖች /አንድ ፋይናንሻል ፕሮፖዛል/ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ/ እና አንድ ቴክኒካል ፕሮፖዛል/አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ/ በሰም በማሸግ እስከ 11/03/2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የጽ/ቤቱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ቴክኒካል ፕሮፖዛል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት እለት በ11/03/2018 ዓ.ም በ4:30 ላይ አዲስ አበባ ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የጽ/ቤቱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ፋይናንሻል ፕሮፖዛል የቴከኒካል ፕሮፖዛል ውጤት ከታወቀ በኋላ ለተጫራቾች የሚጻፍ ደብዳቤ መሠረት ይሆናል::
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋው 1% /አንድ ፐርሰንት/ በ CPO ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. እሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለፀለት በውሉ መሠረት ዕቃዎቹን አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-11-90-73-30/ 09-10-35-70-30 ደውለው ይጠይቁ፡፡
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
