Tender Detail

Tender Details


የሲዳማ ብሔራዊ ክ/መንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በተለያዩ ሎቶች ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ ከህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክ/መንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን


አገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ /NCB/

ጨረታ ቁጥር SIPDC-YIAIP/NCB-/001/18

የሲዳማ ብሔራዊ ክ/መንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በተለያዩ ሎቶች ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ ከህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሱት 1 የጽዳት ዕቃዎችን

ሱት 2 የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን

ሱት 3 የፈርኒቸር ዕቃዎችን

ሱት 4 የደንብ ልብስ

ሱት 5 ሞተር ሳይክል

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሕጋዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ ዕሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በአየር ላይ ይቆያል።

4. የጨረታ ሠነዱ በኮርፖሬሽኑ በግዥ አቅርቦት ኬዝ ቲም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ8፡ዐዐ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል። ዘግይተው የሚመጡ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

5. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው ውል ባለመፈጸም የታገዱ መሆን የለባቸውም።

6. በጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀን ድረስ በኮርፖሬሽኑ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች በዓይነትም ሆነ በመጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሣተፍ ይችላሉ።

8. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO/ BID Bond ለ90 ቀን በኮርፖሬሽኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

 

9. የውል ስምምነት የማይተገብር ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል።

10. በጨረታውን ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ ኮርፖሬሽኑ ተጠያቂ አይሆንም።

11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ መስጠት ክልክል ነው።

12. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን ይኖርበታል።

13. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገጽ ላይ ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም፤ ሙሉ አድራሻቸውን ማኖር አለባቸው።

14. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ለሚኖራቸው ጥያቄ እና ማብራሪያ የጨረታ ጊዜው ከመጠናቀቁ /10/ አስር ቀን በፊት ከታች በተገለጹት ስልከ ቁጥሮች እና አድራሻ በመደወልና በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።ሆኖም ጥያቄው ወይም ማብራሪያው በጽሁፍ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡

15. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥራችን፦ 0954446961/0462125978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፦ /ፒያሳ በሚገኘው አዋሽ ባንከ አ.ማ ሕንፃ 6ኛ (ስድስተኛ) ፎቅ - ሀዋሳ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

Save Tender