Tender Detail

Tender Details

  • Company በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
  • Address ቤቴል ፖስታ ቤት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline02 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-12-02 00:00:00
  • Categories Building Construction , Building Construction , Construction Works , Contractors

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ አማካሪዎችን እና ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት


 

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ 001/2018

 

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ አማካሪዎችን እና ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሸነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

የፕሮጀክት ስም

ወረዳ

የተቋራጭ ደረጃ

የአማካሪ ደረጃ

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

ተቋራጭ

አማካሪ

1

ረጲ ጃፓን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጂ+4 አድሳት ስራ እና ጂ+1 እድሳት ስራ፣ መፀዳጃ ቤት እድሳት፣ የውስጥ አጥር ስራ እና ሳይት ስራ

11

ደረጃ GC 6/BC 5 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጭ

ደረጃ 3 እና ከዛ በላይ የሆነ አማካሪ

 

 

 

450,000 ሺህ ብር

30,000 ብር

 

 

 

 

 

 

 

 

90 ቀን

2

ረጲ ጃፓን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጂ+4 ማስፋፊያ ግንባታ ስራ እና የአጥር ግንባታ ስራ ተያያዥ ስራዎች

11

ደረጃ GC 5/BC 4 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጭ

ደረጃ 3 እና ከዛ በላይ የሆነ አማካሪ

30,000 ብር

3

ወረዳ 4 ጂ+5 ጤና ጣቢያ ማስፋፊያ እና አጥር ስራ ሳይት ዎርከ እና ተያያዥ ስራዎች

04

 

ደረጃ 3 እና ከዛ በላይ የሆነ አማካሪ

30,000 ብር

4

ወረዳ 04 ሼድ ግንባታ ሎት 01

04

ደረጃ GC 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጭ

በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ 1 እና 2 የሆነ አማካሪ

200,000 ሺህ ብር

10,000 ብር (ከተደራጁበት ወረዳ ዋስትና)

5

ወረዳ 04 ሼድ ግንባታ ሎት 02

04

ደረጃ GC 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጭ

በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ 1 እና 2 የሆነ አማካሪ

 

 

 

200,000 ሺህ ብር

10,000 ብር (ከተደራጁበት ወረዳ ዋስትና)

6

ወረዳ 1 ደይ ኬር ግንባታ

01

ደረጃ GC 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጭ

በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ 1 እና 2 የሆነ አማካሪ

10,000 ብር (ከተደራጁበት ወረዳ ዋስትና)

7

ወረዳ 3 ደይ ኬር ግንባታ

01

ደረጃ GC 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጭ

በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ 1 እና 2 የሆነ አማካሪ

10,000 ብር (ከተደራጁበት ወረዳ ዋስትና)

 

  1. ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ያላቸው እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ አማካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል (ከገቢዎች) ማቅረብ የሚችሉ ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (egp)፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማ የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል። በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ፤ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከታች በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
  3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሃያ አንድ ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት (Calendar Days) የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 2ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 204 ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በምህንድስና ግዥ ቡድን በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱት ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው የመቁጠሪያ ቀን (Calendar Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 22 ኛው የሥራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
  5. ተጫራቾች ለ 90 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE/ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
  7. ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
  8. በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያ በሚያዘው መሠረት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ ፡-

አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በመረጠው አንድ ሎት ብቻ ይሆናል። በአንድ ሎት በላይ ተወዳድሮ የተገኘ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል።

የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 2ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 204 ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ምህንድስና ግዥ ቡድን በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ቤቴል ፖስታ ቤት

 

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት

 

Save Tender